image
image
image
image
image

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል እና ኪነ ጥበብ ቢሮ ባለፉት ሶስት ወራት ያከናወናቸውን ስራዎች የክ/ከተማ ባህል እና ኪነ ጥበብ ጽ/ቤት ኃላፊዎች በተገኙበት በዛሬው ዕለት ገመገመ።

ጥቅምት 6, 2018
ባለፉት ሶስት ወራት የተከናወኑ የቁልፍና የመደበኛ ስራዎች አፈጻጸምን አስመልክተው ሪፖርት ያቀረቡት የቢሮው ዕቅድና በጀት ዝግጅት፣ ክትትል ግምገማ ዳይሬክቶሬት የሆኑት አቶ ዘመነ ጥጋቡ ባለፉት ሶስት ወራት የተከናወኑ ቁልፍና መደበኛ ስራዎች አፈጻጸምን በዝርዝር አቅርበዋል። ሪፖርቱ ከአገልግሎት አሰጣ፣ ከመልካም አስተዳደርና ከመደበኛ ስራዎች አፈጻጸም ጋር በተያያዘ የተከናወኑ ስራዎችን መሰረት በማድረግ የቀረበ ሲሆን በአፈጻጸም ሂደት የነበሩ ጥንካሬዎችና ውስንነቶች እንዲሁም በቀጣይ ሁለተኛ ሩብ አመት ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን ታሳቢ በማድረግ በዝርዝር ቀርቧል። በሪፖርቱ ላይ ባለፉት ሶስት ወራት ከባህል ዕሴት ግንባታ ስራዎች አንጻር፣ ከጷጉሜ ቀናት ከበራ ፣ዘመን መለወጫ እንዲሁም የመስቀልና የኢሬቻ ሀይማኖታዊና ባህላዊ በዓላትን አስመልክቶ የተከናዎኑ ስራዎች አበረታች ውጤት የተመዘገባቸው መሆኑ ተገልጿል። በተመሳሳይ መልኩ አሰባሳቢና የወል ትርክት ግንባታን ለማስረጽ በሚያስችል መልኩ ተዘጋጅተው ለህብረተሰቡ ተደራሽ የሆኑ የኪነ ጥበብ ስራዎች ውጤት የተመዘገበባቸው መሆኑ ተመላክቷል። በመድረኩ ላይ ተገኝተው ከተሳታፊዎች የቀረቡ ጥያቄዎችና አስተያየቶችን መሰረት አድርገው የማጠቃለያ ሀሳብ የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል እና ኪነጥበብ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ዶ/ር ሂሩት ካሳው እንደገለጹት ባለፉት ሶስት ወራት ቢሮው በቁልፍ ተግባራትም ሆነ በመደበኛ ስራዎች አፈጻጸም ረገድ አበረታች ውጤቶች ማስመዝገቡን ገልጸው በቀጣይ ሁለተኛ ሩብ ዓመትም ከዚህ የተሻለና ያደገ ውጤት ለማስመዝገብ ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገቡ ጉዳዮች ላይ አጽኖት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች