image
image
image
image
image

የልደታ ክፍለ ከተማ ባህልና ኪነ-ጥበብ ጽ/ቤት የአገልግሎት አሰጣጥ መማክርት ጉባኤ አቋቋመ።

ጥቅምት 1, 2018
የባህልና ኪነጥብብ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ግዛው አለሙ የአገልግሎት አሰጣጥ መማክርት ጉባኤ መቋቋሙ አላማዉ የቢሮዉ ተገልጋዮችና ባለድርሻ አካላት በአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል፣ የሚጠበቅባቸዉን በዉጤታማነት እንዲወጡ የሚያግዝ የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት እና ተግባራዊ ለማድረግ መሆኑን ገልጸዋል። ጉባኤዉ የሚተገብራቸዉ የሚወጡ መመሪያዎችና ህጎች የህዝቡን ጥቅም የጠበቁ ስለመሆናቸዉ ማረጋገጥ፣ የሚስተዋሉ የአገልግሎት ችግሮች እንዲፈቱ ምክረ ሀሳብ ማቅረብ ፣ ብልሹ አሰራሮችን መጠቆም ፣የተቋሙን አፈጻጸም መከታተል በአጠቃላይ የህዝቡ ድምጽ በመንግስት እንዲደመጥ ድልድይ በመሆን የህብረተሰቡን ተጠቃሚነትንና እርካታን ማረጋገጥ መሆኑን ማኑዋሉን ባቀረቡበት ወቅት ገልተዋል። በአገልግሎት አሰጣጥ መማክርት ጉባኤዉ የልደታ ም/ቤት፣ እደጥበብ አምራች፣ ከሲቪክ ማህበራት፣ ከኪነጥበብ በድኖች ማህበራት የተገልጋይ መማክርት ስራዉን የሚመሩ ስራ አስፈጻሚዎችም ተመርጠዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች