image
image
image
image
image

የልደታ ክፍለ ከተማ ባህልና ኪነ_ጥበብ ጽ/ቤት "ዘላቂ ልማት ለሀገራዊ ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የማንሰራራት ቀንና የታላቁን የህዳሴ ግድብ መመረቅ ምክንያት በማድረግ ልዩ ልዩ ኪነ ጥበባዊ ስራዎችንና ሁነቶችን በማቅረብ ቀኑን አክብሯል።

መስከረም 2, 2018
የክ/ከተማው ባህልና ኪነ_ጥበብ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግዛው አለሙ በማንሰራራት ቀን በድምቀት የተመረቀው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውስጥና የውጭ ጠላቶችን አንገት ያስደፋንበትና ብልጽግናችን ዕውን እንደሚሆን ያሳየንበት ዳግማዊ አድዋችን ነው” ብለዋል፡፡ ህዳሴ ግድብ የጋራ መለያ አርማችን ኢትዮጵያ መሻገርና ማንሰራራት እንደምትችል ለአለም ያስተማርንበት ግድብ ነው ያሉ ሲሆን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ተሰርቶ መጠናቀቁ በአንድነት ተባብረን ከሰራን ትልቅ ትምህርት የምንወስድበት ነው ብለዋል። የኪነጥበብ ምሽቱ በሜክሲኮ አደባባይ የተካሄደ ሲሆን የተለያዩ ኪነጥበባዊ ዝግጅቶች ለታዳሚያን የቀረቡ ሲሆን፣ የተለያዩን የኅብረተሰብ ክፍሎች በመድረኩ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች