image
image
image
image
image

"የጥበብ ስጦታ ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል 17ኛው አዲስ የኪነጥበብ ፌስቲቫል የማስጀመርያ መርሀግብር ተካሄደ።

መጋቢት 6, 2018
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል እና ኪነጥበብ ቢሮ "የጥበብ ስጦታ ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል 17ኛው አዲስ የኪነጥበብ ፌስቲቫል ከመጋቢት 05 እስከ 07/2018 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ በድምቀት ተከፈተ። ​ቢሮው አመታዊ የጥበብ ድግስ የከተማችንን የኪነ-ጥበብ ሀብቶች አጉልቶ ለማሳየት የተዘጋጀ ሲሆን፣ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣የሀይማኖት አባቶች፣አበገዳዎች፣ሀደስንቄዎች፣አንጋፋና ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎችና ከአስራ አንዱም ክ/ከተማ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት 17ኛው አዲስ የኪነጥበብ ፌስቲቫል በድምቀት እየተካሄደ ይገኛል። በፌስቲቫሉ ላይ ማራኪ የኪነ-ጥበብ ውድድሮች፣ ዐውደ ርዕዮች እና ልዩ ልዩ ሥነ-ጥበባዊ ክዋኔዎች፣ በዕይታዊ፣ በክውን እና በሥነ-ፅሑፋዊ ጥበባት መስኮች የተዘጋጁ አዝናኝ እና አስተማሪ ሥራዎች እየቀረቡ ሲሆን በመርሀግብሩ ላይ በከተማዋ የሚገኙ የሥነ-ጥበብ ተቋማት፣ ቴአትር ቤቶች፣ የአ.አ.ዩ የሥነ-ጥበብ ትምህርት ቤቶች፣ የሀይማኖት ተቋማት፣ ከ11ዱም ክፍለ ከተሞች የተወጣጡ ባለሙያዎች፣ ትምህርት ቤቶች እና የሙያ ማህበራት በአንድ መድረክ ላይ እንደሚታደሙ የዝግጅት ክፍሉ አስታውቋል። ​የአዲስ አበባ ባህል እና ኪነጥበብ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ዶክተር ሂሩት ካሳው በመድረኩ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት ኪነጥበብ የሀገርን ታሪክ ከመዘከር እና ማንነትን ከመቅረፅ ባለፈ፤ ልዩነቶችን አቻችሎ ሰዎችን በአንድነት የሚያስተሳስርና መግባባትን የሚፈጥር ዓለም አቀፍ ቋንቋ ነው ካሉ በኋላ የጥበብ ባለሙያዎች የተዛቡ አመለካከቶችን በማረም፣ መልካም እሴቶችን በማንቃት እና ማህበረሰብን ለሀገር ከፍታእና ብልፅግና በማስተባበር ሀገርን ወደ ተሻለ ደረጃ የማድረስ ትልቅ ኃላፊነትና የመሪነት ሚና እንዳላቸው አሳስበዋል። ቢሮ ኃላፊዋ አያይዘውም ይህ ፌስቲቫል የጥበብ ስራዎችን ለማየት ብቻ ሳይሆን የህዝቦችን ወንድማማችነትና አንድነት ለማጉላት የተዘጋጀ ነው ብለዋል ። በኪነጥበብ በመተሳሰብ እና በጋራ በመስራት የኢትዮጵያን ብልፅግና እና ከፍታ ማረጋገጥ ይቻላል! ካሉ በኋላ ይህንን ታላቅ ፌስቲቫል መላው የከተማዋ ነዋሪዎች፣ የኪነጥበብ አድናቂዎች፣ የጥበብ ባለሙያዎች እንዲሁም ሁሉም የሚዲያ ተቋማት በመስቀል አደባባይ ተገኝታችሁ የጥበብን ድግስ እንድትታደሙ በአክብሮት በመጋበዝ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች

የባህልና ኪነ-ጥበብ ጽ/ቤት
የማዕከል አመራሮቻችን
  • የባህልና ኪነ-ጥበብ ጽ/ቤት
  • ህዳር 22, 2018
የባህልና ኪነ-ጥበብ ጽ/ቤት
ዶክተር ሂሩት
  • የባህልና ኪነ-ጥበብ ጽ/ቤት
  • ሀምሌ 22, 2018