image
image
image
image
image

በአስራ አንዱ ክ/ከተሞች መካከል በተካሄደው ከተማ አቀፍ አዲስ የኪነ ጥበብ ፌስቲቫል ዉድድር በአጠቃላይ አፈጻጸም የልደታ ክ/ከተማ ሁለተኛ በመዉጣት የአዋርድ ተሸላሚ ሆነ።

መጋቢት 9, 2018
"የጥበብ ስጦታ ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የነበረው ከተማ አቀፍ አዲስ የኪነ ጥበብ ፌስቲቫል ሳምንት ተጠናቀቀ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል እና ኪነ-ጥበብ ቢሮ "የጥበብ ስጦታ ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል ለተከታታይ ሶስት ቀናት በመስቀል አደባባይ በድምቀት ሲያካሂድ የነበረው 17ኛው ከተማ አቀፍ አዲስ የኪነ ጥበብ ፌስቲቫል በዛሬው ዕለት ተጠናቋል። በፌስቲቫሉ ከ16 በላይ የሚሆኑ አዝናኝና አስተማሪ የኪነ-ጥበብ ስራዎች የቀረቡ ሲሆን ከእነዚህ መካከል ባህላዊና ዘመናዊ የዳንስ ውድድሮች፣ ዓውደ ርዕዮች፣ እንዲሁም በክውንና በሥነ ጽሑፍ የጥበብ መስኮች ተዘጋጅተው የቀረቡ የጥበብ ስራዎች ይገኙበታል። ከተማ አቀፍ አዲስ የኪነጥበብ ፌስቲቫሉ አማተር የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ከነባር የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች የልምድ ልውውጥ የሚያደርጉበት ወሳኝ መድረክ መሆኑ ተገልጿዋል። በፌስቲቫሉ ላይ ተሳትፈው ከ 1- 3ኛ ደረጃ ይዘው ላጠናቀቁ የውድድሩ ተሳታፊዎች የገንዘብ፣ የሙያ መርጃ መሳሪያዎች፣ የዕውቅናና የሰርተፍኬት ማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። በመጨረሻም በአስራ አንዱ ክ/ከተሞች መካከል በተካሄደው ውድድር በአጠቃላይ አፈጻጸም አንደኛ የካ ክ/ከተማ፣ ሁለተኛ ልደታ ክ/ከተማ ፣ሶስተኛ ንፍስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ በቅደም ተከተል የአዋርድ ተሸላሚ ሁነዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች

የባህልና ኪነ-ጥበብ ጽ/ቤት
የማዕከል አመራሮቻችን
  • የባህልና ኪነ-ጥበብ ጽ/ቤት
  • ህዳር 22, 2018
የባህልና ኪነ-ጥበብ ጽ/ቤት
ዶክተር ሂሩት
  • የባህልና ኪነ-ጥበብ ጽ/ቤት
  • ሀምሌ 22, 2018