image
image
image
image
image

“ብዝኃነት የኢትዮጵያ ጌጥ” በሚል መሪ መልእክት የኅብር ቀንን አስመልክቶ የተለያዩ ኪነ-ጥበባዊ ዝግጅቶች ተካሄደ።

መስከረም 2, 2018
በልደታ ክ/ከተማ ባህል ና ኪነ-ጥበብ ጽ/ቤት አዘጋጅነት ጳጉሜ 2 የኅብር ቀንን አስመልክቶ "ብዝኀነት የኢትዮጵያ ጌጥ" በሚል መሪ መልዕክት በተለያዩ ኪነ-ጥበባዊ ዝግጅቶች ተካሂዷል። ዝግጅቱን በንግግር ያስጀመሩት አቶ አሰፋ ቶላ በልደታ ክ/ከተማ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ምክትል ሀላፊ ሲሆኑ ጥንታዊና ገናና ታሪክ ካላቸዉ፣ የበርካታ እና ማራኪ ብዝኃ ሕይወት ባለቤቷ ኢትዮጵያ ብዝኃ ማንነት፣ ባህል፣ ቋንቋ፣ ሃይማኖት ያላቸውና ተፈቃቅደዉ በጋራ ታሪክ እየሠሩ የቀጠሉ ሕዝቦች ሀገር መኾኗን አንስተዋል፡፡ ኢትዮጵያውያንን የሚያስተሳስሩን የጋራ ድሎች እና ታሪኮች አሉን፤ ቀደምቶቻችን በጋራ ጠላትን መክተዉ ነፃ ሀገር አስረክበውናል፡፡ እኛም በጋራ ታላቁ ሕዳሴ ግድብን አሳክተናል፤ በዚህ የወል ድላችን በመስፈንጠር ኢትዮጵያን ወደ ከፍታዋ ማድረስ ይኖርብናል በማለት አቶ አሰፋ አክለው ገልፀዋል፡፡ እንደነዚህ አይነት ኪነ-ጥበባዊ ዝግጅቶች የሀገራችንን መልካም እሴቶች ፍንትው አድርገው የሚያሳዩ ናቸው ያሉት አቶ አሰፋ ኪነ-ጥበብ ለወንድማማችነትና እህትማማችነት እንዲሁም የወል ትርክትን በማፅናት ለሀገረ መንግስት ግንባታ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ስላላቸው መሰል ዝግጅቶች ተጠናክረው መሄድ እንደሚገባቸው ጠቁመዋል። የልደታ ክ/ከተማ የባህልና ዘመናዊ የኪነ-ጥበብ ቡድን በተለያዩ የኪነ-ጥበብ ስራዎች ዝግጅቱን አድምቀውታል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች