image
image
image
image
image

ለቀጣይ ተልዕኮ የሚመጥን የአመራር ቁመና በመላበስ የልደታን ከፍታ ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ።

ጥቅምት 19, 2018
የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር በቀጣይ 10 ቀናት የሚተገበሩ የልማትና መልካም አስተዳደር እቅድ ላይ የክ/ከተማ እና የወረዳ አመራሮች በተገኙበት ውይይት በማካሄድ አቅጣጫ ተቀመጠ። የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ተወካይና የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ጢቂ ድሪባ በመድረኩ ላይ እንዳሉት የህዝብንና የመንግስትን ሀላፊነት በጊዜ የለኝም መንፈስ በመስራት ከተማችን እንዲሁም ክ/ከተማው የያዙትን የልማት እና መልካም አስተዳደር ቁልፍ ተግባራት በቁርጠኝነት በማስፈፀምና በመፈፀም የተጣለብንን ሀላፊነት መወጣይ ይገባል ብለዋል። አቶ ጢቂ አያይዘው ለቀጣይ ተልዕኮ የሚመጥን የአመራር ቁመና በመላበስ የልደታን ከፍታ ለማረጋገጥ የመንግስትና የፓርቲ ተግባራትን በትጋት፣ በቁርጠኝነት፣ በውጤት እና በስነ-ምግባር መምራት እንደሚገባ አሳስበዋል። ይህ አመራር የ2018 በጀት ዓመት በአስተዳደሩ ከተያዙ ስትራቴጂክ ግቦች የተቀዱ የ10 ቀናት ተግባራትን መፈፀምና ማስፈፀም የሚችል የማህበረሰቡን ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ቁርጠኛ የሆነ፤ የሚሰጠውን ተልዕኮ አቀናጅቶ መምራትና ሀላፊነቱ በአግባቡ መወጣት የሚችል መሆን አለበት በመድረኩ አቅጣጫ ተቀምጧል። በመድረኩ ዋነኛ የትኩረት መስክ የሆኑት ሰዉ ተኮር ተግባራት፣ የፀጥታ፣ የስራ እድል ፈጠራ፣ የሌማት ትሩፋት እና የኢንሼቲቭ ስራዎችን ሌሎች የልማትና መልካም አስተዳደር እቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች