image
image
image
image
image

በክፍለ ከተማው ተተኪ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችን ለማፍራት በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።

ጥቅምት 2, 2018
የልደታ ክፍለ ከተማ ባህልና ኪነ-ጥበብ ጽ/ቤት ለአማተር የኪነጥበብ ቡድኖች የኪነ ጥበብ ሙያ ስልጠና ሰጠ። በስልጠና ላይ የልደታ ክ/ከ የባህልና ኪነ ጥበብ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግዛው አለሙ እንደገለጹት ክፍለ ከተማው ለበርካታ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች መፍለቂያ ነው በማለት ይህን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ተተኪ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችን ለማፍራት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በተለያዩ የኪነ- ጥበብ ዘርፎች ተተኪ ከያንያንን ለማፍራት የስልጠናዉ አስተዋጽኦ የጎላ መሆኑን ገልጸው፤ ተተኪ ከያኒያን በዚህ መሠል ስልጠና ማለፍ እንደሚገባቸው ተናግረዋል። የጽ/ቤቱ የኪነጥበብ ማበልጸግ ቡድን መሪ አቶ ሀይላይ ተ/ሚካኤል በበኩላቸው በአማተር የኪነጥበቡ ቡድኖች ተደራጅተው ለሚሰሩ ወጣቶች አስፈላጊውን ድጋፍ እና ክትትል እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል. በስልጠናው የኪነ ጥበብ ምንነት፣ድርሰት፤ትወና፤ ዘውግ ዙሪያ ያተኮረ ሲሆን ብቃት ያለው የኪነ ጥበብ ባለሙያ ለመፍጠር በሁሉም ወረዳ ያሉ ተሰጥኦ ያላቸውን ወጣቶች ማጠናከር ስለሚገባ ስልጠናው መዘጋጀቱንና በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች